·Impact Stories
በሆሳዕና ማረሚያ ተቋም የሚገኙ 15 ሴት ታራሚዎችን በሙያ ሥልጠና አሳልፈን ለምረቃ አበቃን።
በሆሳዕና ማረሚያ ተቋም የሚገኙ 15 ሴት ታራሚዎችን በሙያ ሥልጠና አሳልፈን ለምረቃ ማብቃታችንን ስናበስር በታላቅ ደስታና ኩራት ነው!

በሆሳዕና ማረሚያ ተቋም የሚገኙ 15 ሴት ታራሚዎችን በሙያ ሥልጠና አሳልፈን ለምረቃ ማብቃታችንን ስናበስር በታላቅ ደስታና ኩራት ነው! እነዚህ እህቶቻችን ባለፉት ሦስት ወራት በጽናትና በትጋት ተምረው ለዚህ ስኬት መብቃታቸው ለድርጅታችን ሆፕ ቢሃይንድ ባርስ (Hope Behind Bars) ትልቅ ኩራት ሆኖናል። ባለፉት 10 ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች ድርጅታችን ባለፉት 10 ወራት በ9 ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ባደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴ በርካታ ወገኖችን መድረስ ችሏል፦ 140 ሴቶችን የሥልጠናውና የድጋፉ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። 35 ሕፃናትን በተለያዩ መንገዶች መደገፍ ተችሏል። የዛሬው ምርቃት የድርጅታችን ዋና ዓላማ የሆኑትን ተሃድሶ (Rehabilitation)፣ የመቋቋም አቅም (Resilience) እና መልሶ መቀላቀልን (Reintegration) **በተግባር ያሳየ ደማቅ ኩነት ነበር። 💡 የምናደርጋቸው ተከታታይ ድጋፎች በየሁለት ወሩ፦ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች አቅርቦት። በየሦስት ወሩ፦ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና (ታራሚዎቹ ነገ ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ መሠረት የሚጥል ነው።
ስለሆነም፦ ለሆሳዕና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ለክቡራን አጋሮቻችን እና ለበጎ ፍቃደኞቻችን 🙏 ከልብ የመነጨ ምስጋና ይህ ትልቅ ሥራ ያለ እናንተ ድጋፍ እውን ሊሆን አይችልም ነበር።
